
በቶፓዚዩን ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ፣ በደራሲና ዳይሬክተር አንተነህ አስረስ የተሰራው “በዝምታ” የተሰኘው ፊልም ተመረቆ አዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ሲኒማ ቤቶች ለእይታ ቀርባል፡ ፡ 850 ሺህ ብር እንደፈጀ የተነገረለት ፊልሙ፤የ1፡35 ርዝመት ያለው ልብ አንጠልጣይ የቤተሰብ ድራማ ነው ተብሏል፡፡
በፊልሙ ላይ እንግዳሰው ሀብቴ፣ አንተነህ አስረስ፣ ናሆም ጌታቸው፣ ፀደንያ ኤፍሬም፣ መራዊት ዮሐንስና ሌሎችም ተዋንያን ተሳትፈውበታል፡፡
ምንጭ: Addis Happening