የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ እና በክልል ስታዲየሞች ቀጥለው ይውላሉ።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ እና በክልል ስታዲየሞች ቀጥለው ይውላሉ።

በ7ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአርባምንጭ ከተማ ደደቢት ከሲዳማ ቡና አዲስ አበባ ላይ ይጫወታሉ። የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ እና በክልል ስታዲየሞች ቀጥለው ይውላሉ።

በዚህ ሳምንት ቅዳሜና እሁድ ከሚደረጉ ስምንት ጨዋታዎች መካከል ሁለቱ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲደረጉ ቀሪዎቹ ስድስት ጨዋታዎች ደግሞ በክልል ስታዲየሞች የሚደረጉ ይሆናሉ። ቅዳሜ ደደቢት ከሲዳማ ቡና እሁድ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአርባ ምንጭ ከተማ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ከቀኑ 11:30 ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በክልል ስታዲየሞች ቅዳሜ አዋሳ ከተማ ከድሬዳዋ ከተማ ፣ እሁድ ደግሞ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከመከላከያ፣ ወላይታ ድቻ ከመቀሌ ከተማ፣ አዳማ ከተማ ከፋሲል ከተማ ክልል ላይ በተመሳሳይ 9:00 የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።

ጅማ አባ ጅፋር ከኢትዮጵያ ቡና ሰኞ በጅማ ስታዲየም ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ነው የሚሆነው። ወልዲያ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ የሚያደርጉት ጨዋታ ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ታውቋል።

ፕሪሚየር ሊጉን ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲና ደደቢት በእኩል 10 ነጥብ በጎል ተበላልጠው አንደኛና ሁለተኛ ሆነው ሲመሩ ፋሲል ከተማ፣ አዳማ ከተማ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና ከ3ኛ እስከ 6ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

ፕሪሚየር ሊጉን የኢትዮ ኤሌክትሪኩ አል ሀሰን ካሉሻ በ4 ግቦች ከፍተኛ ጎል አግቢ ሆኖ ሲመራ ኤደም ኮድዞ ከወልዲያ፣ ጃኮ አራፋት ከወላይታ ድቻ፣ ላኪ ሳኒ ከአርባምንጭ ከተማ እንዲሁም ያቡን ዊልያምና ዳዊት ፍቃዱ ከሀዋሳ ከተማ በተመሳሳይ 3 ጎሎች ይከተላሉ።

Source: ENA